<> የህልም እና የዕድል ግጥምጥሞሽ | Amhara Mass Media Agency Skip to main content
የህልም እና የዕድል ግጥምጥሞሽ

አሜሪካዊቷ የ73 ዓመት የዕድሜ ባለፀጋ በሕልማቸው በተመለከቷቸው የሎተሪ ቁጥሮች ለሁለተኛ ጊዜ የ50 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ባለዕድል ሆነዋል፡፡

No photo description available.

ባሕር ዳር፡ ሰኔ 30/2011 ዓ.ም (አብመድ) በአሜሪካ የሜሪላንድ ግዛት ነዋሪ የሆኑት የ73 ዓመት የዕድሜ ባለፀጋ እናት በሕልማቸው በተመለከቷቸው የሎተሪ ቁጥሮች ለሁለተኛ ጊዜ ተመሳሳይ የገንዘብ መጠን ያለው ዕጣ አሸናፊ ሆነዋል፡፡

ባለፈው ሳምንት በወጣው የሜረላንድ ሎተሪ ድርጅት ባለአምስት ቁጥሮች የሎተሪ ዕጣ አዛውንቷ ለሁለተኛ ጊዜ ነው 50 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ባለዕድል የሆኑት፡፡

አዛውንቷ ከዚህ ዕጣ በፊት በቆረጡት የሎተሪ ትኬት 50 ሺህ የአሜሪካ ዶላር አሸንፈው ነበር፡፡ አዛውንቷ ከዚህ ቀደም ባሸነፉበት ተመሳሳይ ቁጥር በድጋሜ ቆርጠው ተመሳሳይ መጠን ያለው ገንዘብ ማሸነፋቸው አነጋጋሪ ሆኗል ነው የተባለው፡፡

ቤተሰቦቻቸው በቂ አቅም እንዳላቸው የገለጹት አዛውንቷ ‹‹ገንዘቡን ቤተሰቦቼ አጥብቀው የሚፈልጉት ቢሆን ኖሮ ባለዕድል ባልሆንኩ ነበር›› ቢሉም ያሸነፉትን ገንዘብ ለቤተሰቦቻቸው ዕርዳታ እንደሚያውሉት ማቀዳቸውን ግን ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፡- ዩ ፒ አይ


በታዘብ አራጋው

Image