<> የአዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ምክትል ሊቀ መንበርና ዕጩ ርዕሰ መስተዳድር ሰየመ፡፡ | Amhara Mass Media Agency Skip to main content
የአዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ምክትል ሊቀ መንበርና ዕጩ ርዕሰ መስተዳድር ሰየመ፡፡

 

ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 8/2011 ዓ.ም (አብመድ) የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) አቶ ዮሐንስ ቧያለውን የፓርቲው ምክትል ሊቀ-መንበር እና አቶ ተመስገን ጥሩነህን ደግሞ ዕጩ ርዕሰ መስተዳደር አድርጎ መርጧል።

Image may contain: 1 person, sitting

በተጨማሪም አቶ ተመስገን ጥሩነህና አቶ አገኘው ተሻገር የአዴፓና የኢህአዴግ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ሆነው ተመርጠዋል፡፡

አቶ ተመስገን ጥሩነህ ከዚህ በፊት የምሥራቅ ጎጃም ዞን ዋና አስተዳዳሪ፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ (ኢመደኤ) ዋና ዳይሬክተር እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንነት ጉዳዮች አማካሪ ሆነው ማገልገላቸው ይታወቃል።

Image may contain: 1 person

አቶ አገኘሁ ተሻገር ደግሞ የቀድሞው ሰሜን ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ፣ የአማራ ሥራ አመራር አካዳሚ ዋና ዳይሬክተር፣ የንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ማገልገላቸው የሚታወቅ ነው፡፡ በዚህ ወቅት ደግሞ የክልሉ ሕዝብ ሠላምና ደኅንነት ቢሮ ኃላፊ ሆነዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ታርቆ ክንዴ

Image
The website encountered an unexpected error. Please try again later.