<> Skip to main content
በባቡር አገልግሎቱ መቆራረጥ እየተጉላሉ መሆኑን ተገልጋዮች ተናገሩ፡፡

 

የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማኅበር ደግሞ በውስጣዊ ችግር ምክንያት አንድም ባቡር ቆሞ አያውቅም ብሏል፡፡

አስተያዬታቸውን ለኢዜአ የሰጡ ተገልጋዮች የምድር ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎቱ በሚቋረጥበት ጊዜ አንዳንድ ጊዜም ስለተፈጠረው ሁኔታ መረጃ የሚሰጣቸው አካል አለመኖሩን ተናግረዋል፡፡
የባቡሩ
የፍጥነት አቅም መገደቡንና ከአዲስ አበባ ድሬዳዋ በአራት ሰዓት ይደርሳል የተባለው ባቡር እስከ አስር ሰዓት እየወሰደበት እንደሆነም ነው የተናገሩት፡፡ ከዚህ በፊት ግን
ዘገየ
ቢባል በስድስት ሰዓታት ይደርስ እንደነበርም ነው አስተያዬት የሰጡት፡፡
ሻንጣዎችን
የሚጭንና የሚያወርድ ሠራተኛ አለመኖርም ሌላው ችግር መሆኑን አንስተዋል፡፡

የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማኅበር ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ጥላሁን  ችግሮች መኖራቸውን አምነዋል፡፡ በፀጥታ ችግር ምክንያት የባቡር ሀዲዱ ሲዘጋ እና  ተያያዥ ችግሮች ሲፈጠሩ ጉዳዩ የሚመለከተው የጸጥታ መዋቅሩ ስለሆነ ጉዳዩን እስኪጣራ ድረስ ምድር ባቡር መረጃ እንደማያገኝም ነው የተናገሩት። ‹ለምን እንደሚዘገይ መረጃ አይደርሰንም› የተባለው የመረጃ እጥረት ስለሚገጥም እንጂ መንገደኞችን መረጃ ለመከልከል ተብሎ የተደረገ አለመሆኑንም ኢንጂነር ጥላሁን አስረድተዋል፡፡
 

‹‹በኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማኅበር ውስጣዊ ችግር ምክንያት አንድም ባቡር ቆሞ አያውቅም፤ ችግሮች የሚፈጠሩት በኃይል መቆራረጥ፣ በጸጥታ ችግሮች እናተያያዥ ጉዳዮች ነው›› ብለዋል ኢንጂነር ጥላሁን፡፡ በየትኛውም ዓለም በባቡር አገልግሎት የሻንጣ ጫኝና አውራጅ ተቀጣሪ ሠራተኞች አለመኖሩንና ምድር ባቡሩም አገልግሎቱን እንደማይሰጥ የተናገሩት  የአክሲዮን ማኅበሩ ዋና ዳይሬክተር ቅሬታው ተገቢነት እንደሌለው አስረድተዋል፡፡

ትላልቅ ሻንጣዎችንና የኮንትሮባንድ እቃዎችን የሚይዙ ተሳፋሪዎች መኖራቸውን የተናገሩት ዋና ዳይሬክተሩ ይህ አግባብነት እንደሌለው ነው ያሳሰቡት፡፡ ለእቃ መጫኛ የተዘጋጁ ባቡሮች ስላሉ ከኪሎ በላይ ለሆኑ እቃዎች የዕቃ መጫኛ ባቡሮችን  እንዲጠቀሙም አሳስበዋል።

ባቡሩ በሚፈጠሩ የተለያዩ ችግሮች ምክንያት የፍጥነት ገደቡ ውስን በመሆኑ ዘግይቶ በመድረሱ የሚፈጠሩ መጉላላቶችን ለመቅረፍ እየሰሩ መሆኑንም አክሲዮን ማኅበሩ ዋና ዳይሬክተር አስታውቀዋል፡፡

ተሳፋሪዎች ምቹ ጉዞ እንዲኖራቸው በጥናት ላይ የተመሠረቱ ሥራዎችን እንደሚሰሩም ኢንጂነር ጥላሁን ገለጸዋል፡፡

751 ነጥብ 7 ኪሎ ሜትር የሚረዝመው የአዲስ አበባ ጅቡቲ የባቡር መስመር ጥር 1/2018 (እ.አ.አ.) ሥራ መጀመሩ ይታወሳል፡፡

 

ፎቶ፡- ከድረ ገጽ

Top of Form

Bottom of Form

 

Image