<> Skip to main content
የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ወደ መምህርነት ሙያ የሚገቡ ተማሪዎች

የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ወደ መምህርነት ሙያ የሚገቡ ተማሪዎች ብቁ መሆን እንዳለባቸው ተገለጸ፡፡

ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 06/2011 ዓ.ም (አብመድ) የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚገቡና በመምርነት ሙያ የሚሰለጥኑ ተማሪዎችን ውጤትን መሠረት በማድረግ መመልመል እንደሚገባ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ተማሪዎችን ለመምህርነት ለመመልመል ከፍተኛ ውጤት እና ፍላጎት ሊኖራቸው እንደሚያስፈልግ ነው የትምህርት ሚኒስቴር የ2011 በጀት ዓመት ሪፖርቱን ባቀረበት ወቅት ያስታወቀው፡፡

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የቅድመ መደበኛ ትምህርትና የጎልማሶች ትምህርት ላይ በቂ ሥራ አለመሠራቱም ተጠቁሟል፡፡

በተለይም በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ምክንያቶች ወደ 1 ነጥብ 6 ሚሊዮን የሚሆኑ ተማሪዎች ትምህርት ማቋረጣቸው ተገልጿል፤ በቀጣይ መፍትሔ እንደሚበጅለትም ተነግሯል፡፡


a
የትምህርት ማቋረጥ በሚበዛባቸው አካባቢዎች የትምህርት ቁሳቁስ ማሟላት፣ የትምህርት ቤት ምገባ እና ሌሎች ድጋፎችን ለተማሪዎች ለማድረግ እንደሚሠራ የትምህርት ሚኒስትሩ ጥላዬ ጌቴ (ዶክተር) አመልክተዋል፡፡
የኢ.ፕ.ድ ኢብኮን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው በ2012 በጀት ዓመት መምህራን የሚያነሷቸውን ጥያቄዎች ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ለመመለስ እንደሚሠራ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስታውቋል፡፡
በተለይም የመምህራንን ጉዳይ በተመለከተ ከመምህራን ማኅበር ጋር በመተባበር ጥናት እየተካሄደ መሆኑንና ጥናቱ እንዳለቀ ውጤቱ ይፋ እንደሚደረግም ተገልጿል፡፡
15 ሺህ የሚሆኑ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራንን ለአዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ ለማብቃት ስልጠና መስጠት እንደሚጀመርም ተጠቅሷል፡፡

Image