<> Skip to main content
ኢትዮጵያ እየወሰደች ባለው ምጣኔ ሀብታዊ ማሻሻያ ዙሪያ የዘርፉ ምሁራን እየመከሩ

ኢትዮጵያ እየወሰደች ባለው ምጣኔ ሀብታዊ ማሻሻያ ዙሪያ የዘርፉ ምሁራን እየመከሩ ነው ተብሏል፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የሚዘጋጀው የአዲስ ወግ የውይይት መድረክ በምጣኔ ሀብት ማሻሻያዎችና እየገጠሙ ባሉ ፈተናዎች ዙሪያ ትኩረት አድርጎ እየመከረ ነው፡፡

የፋይናንስ ሚኒስትሩ ከፍተኛ አማካሪ ብሩክ ታዬ ባለፉት 17 ወራት የተተገበሩ አንኳር የማሻሻያ ሥራዎችን ዘርዝረዋል።

በዚህም ዘላቂ መፍትሔ የሚሹ የዋጋ ግሽበት፣ የውጭ ምንዛሬ እጥረትና የብድር አከፋፈልን የተመለከቱ ፖሊሲዎች፣ በንግድ ውስጥ ላሉና ወደ ንግድ ለሚመጡ ማነቆዎችን መፍታትና የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን ወደ ግል ለማዞር እንቅስቃሴዎች መደረጋቸውን ጠቅሰዋል።

a

ኢብኮ እንደዘገበው ከአበዳሪዎች ጋር በመደራደር እፎይታ ለማግኘት የሚያስችሉ ማሸጋሸጊያዎችን ማድረግ፣ ያላለቁ የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን ማስጨረስና ሕጎችን የማብላላትና የመከለስ ሥራዎች መሠራታቸውንም አንስተዋል።

አቶ መሳይ ታደሰ ደግሞ የፋይናንስ አቅርቦት ላይ ያሉ መልካም አጋጣሚዎችንና ፈተናዎችን ባነሱበት ንግግራቸው ለሀገር ውስጥና ለውጭ ሀገር ባለሀብቶች በሚኖር የብድር አቅርቦት እጥረት ዙሪያ መሠራት እንዳለበት አመልክተዋል።

የንግድ እንደራሴ የሆኑት አቶ ብሩክ ፍቅሩ እንደገለፁት ደግሞ በወጭ ንግድ ላይ ዓለም አቀፍ አሠራርን የመረዳት ክፍተት ችግሮች ባጋጠሙ ወቅት ሙሉ በሙሉ መርምሮ የመረዳት አቅም ማዳበር አልተቻለም።

የሕግና የአሠራር ማዕቀፎችም ባለሀብቶችንና የተወሰኑ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ብቻ ሳይሆን ግለሰቦችንም መሠረት ያደረጉ እንዲሆኑ መሥራትና የተሻለ ዕቅድ ማስተባበር አስፈላጊ መሆኑን መክረዋል።

Image