<> Skip to main content
በጎንደር እና አካባቢዋ የተፈጠረውን የሰላም እጦት ወደ ነበረበት ለመመለስ ማህበ

ባሕር ዳር፡ የካቲት 02/2011ዓ.ም (አብመድ) ሰሞኑን በማዕከላዊ ጎንደር በተፈጠረ የሰላም መደፍረስ የሰው ህይወት ጠፍቷል፤ንብረት ወድሟል፤ንጹሃን ዜጎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል፡፡Image may contain: 1 person, standing, ocean, outdoor and water

በወቅታዊ የጎንደር እና አካባቢዋ ሁኔታ በተመለከተ የአማራ ክልል መንግስት መግለጫ ሰጥቷል፡፡ መግለጫውን የሰጡት የአማራ ክልል የመንግስት ኮሚዩንኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ አሰማኸኝ አስረስ አካባቢውን የብጥብጥ እና የሁከት ቀጣና ለማድረግ ሌት ከቀን ሴራ የሚተበትቡ ቡድኖች አሉ ብለዋል፡፡

ዳይሬክተሩ እንዳሉትም ጥር 24 2011ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ወረዳዎች በተነሳው ብጥብጥ የሰው ህይዎት አልፏል፤ንብረት ወድሟል፤ ነዋሪዎችም ከቀያቸው ተፈናቅለዋል፡፡

በምስራቅ ደምቢያ ፣በጭልጋ እና በላይ አርማጭሆ ወረዳዎች ችግሮች ተፈጥረዋል፤ ጥር 30 2011 ዓ.ም ደግሞ በጎንደር ከተማ አስተዳደር በተነሳ አደጋ ከ50 በላይ የቀንድ ከብቶች ሞተዋል ነው ያሉት አቶ አሰማኸኝ፡፡ በአነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ተደረጅተው ሲያደልቡ የነበሩ ወጣቶች ናቸው ከብቶቹ የተቃጠሉባቸው፡፡

‹‹አማራው ሲፈናቀል ከቅማንት ቤት ይጠለላል፤ ቅማንቱ ሲፈናቀል ደግሞ ከአማራ ቤት ይጠለላል፤ ግጭቱ ሁለቱንም ህዝቦች አይወክልም ብለዋል፡፡

ችግሩን እየፈጠረው ያለው ባለፈው ጊዜ ተጠቃሚ የነበረ አሁን ላይ ጥቅሙ የተነካበት የተደራጀ ቡድን ነው ብለዋል፡፡ 
ችግሩ በተነሳባቸው አካባቢዎች የትራንስፖርት እንቅስቃሴ እንደተዘጋም አቶ አሰማኸኝ በመግለጫቸው አንስተዋል፡፡

በጎንደር ከተማ አስተዳደር በተፈጠረው ችግር ፖሊስ ጉዳዩን እያጣራው እንደሆነም አንስተዋል፡፡ በምስራቅ ደምቢያ አካባቢ በዛሬ ውሎ አንጻራዊ ሰላም ቢኖርም ውጥረቱ እንደነገሰ ነው፤ ለዚህ ደግሞ ህዝቡ ከመንግስት ጋር በመሆን ሰላም እንዲመጣ መስራት እንዳለበት ጠይቀዋል፡፡

የተፈናቀሉ ዜጎችን በዘላቂነት ለማቋቋም መንግስት ከህዝቡ ጋር በመሆን እየሰራ ነው ብለዋል ዋና ዳይሬክተሩ፡፡

ዘጋቢ፡-ታርቆ ክንዴ

Image
The website encountered an unexpected error. Please try again later.