<> የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት (አብመድ) | Amhara Mass Media Agency Skip to main content

as 

የአማራ  ብዙኃን መገናኛ ድርጅት

(አብመድ)  

የአማራ  ብዙኃን መገናኛ ድርጅት(አብመድ) በ1993 ዓ/ም የተቋቋመ ሚዲያ ሲሆን ተጠሪነቱ ለክልሉ ምክር ቤት ነው፡፡ድርጅቱ የተቋቋመበት ዓላማ የክልሉን ባህል፣ወግ ፣እሴት በማጠናከር እና ሁለንተናዊ መቀራረብን በመፍጠር የክልሉን ህዝቦች ወደ ተሻለ ልዕልና ማድረስ ነው፡፡በሀገሪቱ ሰላምና ዴሞክራሲ እንዲሰፍን የበኩሉን ሚና እየተወጣ ያለ ሚዲያ ነው፡፡ በስሩም ከአማርኛ በተጨማሪ  በ5 ቋንቋዎች ማለትም  በህምጥኛ፣አዊኛ እና ኦሮምኛ እንዲሁም በእንግሊዝኛ ቋንቋዎች ስርጭቱን ለአድማጭ፣ለተመልካችና አንባቢ  እያደረሰ ይገኛል ፡፡

 

የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ዘመኑ የሚፈልገውን መረጃ ባደራጀው መረብ -(ድረ-ገጽ)  ማንኛውንም ክንውኖቹን ለአንባብያኑ ያደርሳል፡፡ የማሰራጫ ጣብያዎቹም፡-አማራ ሬድዮ 801 ኪሎ ኸርዝ፣ኤፍኤም ባህር ዳር 96.9፣ደሴ ኤፍ ኤም 87.9፣ደብረ ብርሃን ኤፍኤም 91.4፣አማራ ቴሌቪዥን፣በኩር ጋዜጣ እና www.amharaweb.com/Amhara Mass Media Agency(facebook) ናቸው፡፡

ዓለም በኤሌክትሮኒክስ ሚዲያው እጅጉን እየዘመነ በመጣ ቁጥር  አብመድም ከጊዜ ወደ ጊዜ ራሱን እያሻሻለና እያዘመነ መጥቶ በክልሉ መንግስት ልዩ ድጋፍ በከፍተኛ ወጭ የቴሌቪዥን ጣቢያ አቋቁሞ  በማዘመን የቪዲዮ ወል(VIDEO WALL)፣የዲኤም ኤንጂ(DMNG)፣የዲኤስ ኤን ጂ (DSNG)ቴክኖሎጂዎች ተጠቃሚ ሆኗል፡፡እነዚህን ቴክኖሎጂዎች ታጥቆ ፍትሃዊ እና ሚዛናዊ መረጃዎችን ለህዝብ ያደርሳል፡፡

የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ዘጋቢ ዝግጅቶችን፣ማስታወቂያዎችን፣የቀጥታ ስርጭቶችን የሚያቀርብ ሲሆን በእርስዎ ፍላጎት ይሰራል፣ያዘጋጃል፡፡

ድርጅቱን በአጭሩ በዚህ መልክ ካስቀኘናችሁ ታሪኩና የእድገት አቅጣጫው ደግሞ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

a

 

 

የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት

ትናንትና ዛሬ ነገ

ክፍል 1

“ጅማሮ”

 

 

 

 

 

ሃገራችን በ1983 ዓ/ም ወደ አዲስ የድል ምዕራፍ መሸጋገሯ ዛሬ የደረሰችበትን የለውጥ ዘመን በውል እንድታጣጥም ትልቅ መሠረት ጥሏል፡፡ ይህን የድል ብርሃን ተከትሎ በመላ ኢትዮጵያ የተበሰረው የሽግግር ዘመን  ለዓመታት በጦርነቱ ሲዳክሩ ለነበሩት የሃገራችን ክልሎች የትንሣኤ ዘመናቸውን ያመላከተ ነበር፡፡

 

 

 

የሽግግሩን ዘመን ድል ተቋድሰው በጊዜው በሁለት እግራቸው ለመቆም ከሚታትሩ ክልሎች አንዱ የነበረው የአማራ ክልል 1985 ዓ/ምን ተንተርሶ በበርካታ የመልሶ ግንባታ ስራዎች ላይ የተጠመደበት ጊዜ ነበር፡፡

 

 

የክልሉ መንግስት በዋናነትም የክልሉን ሠላም ማረጋገጥ ፣ ክልሉን እንደገና ማደራጀት፣ የክልሉን ልማት ሊያፋጥኑ የሚችሉ ፈፃሚ መ/ቤቶችን ለማቋቋም አልሞ መንቀሣቀስ ቀዳሚ ተግባሩ አደረገ፡፡

 

እናም ያኔ ነው እንግዲህ ለዛሬው የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት መወለድ ምክንያት የሆነው ማስታወቂያ ቢሮ ከአዳዲሶቹ ክልላዊ ቢሮዎች አንዱ በመሆን የተቋቋመው፡፡

 

 

 

በክልሉ ውስጥ የሚዲያ ስራ ይስፋፋ ዘንድ ትልቅ ተልዕኮን የተሰጠው  ማስታወቂያ ቢሮ ገና ከጅማሮው ክልሉ የተሰጠውን ኃላፊነት  ይወጣ ዘንድ 3ት መምሪያዎች በስሩ እንዲደራጅ ተደረገ፡፡  የሬዲዮና ቴሌቪዥን ፣ የኘሬስና የህዝብ ግንኙነት እንዲሁም የዜና አገልግሎት መምሪያዎች፡፡

 

3ት መምሪያዎችን ያቀፈው  ማስታወቂያ ቢሮ  በተቋቋመ ማግስት የተሰጠውን ተልዕኮ ለመወጣት መንቀሣቀስ ሲጀምር በክልሉ ውስጥ በሚዲያ ዘርፍ የሰለጠነ የሰው ሃይል አለመኖር ከጅምሩ ዋነኛ  ችግሩ ሆነ፡፡

 

የባለሙያዎች ከአዲስ አበባ መምጣት የሚዲያ ስራውን በክልሉ  እንዲጀመር  በር ቢከፍትም የተሟላ መሣሪያም ሆነ የተሟላ የስራ ቦታ አለመኖር የሚዲያ ስራ ጅማሮውን አጣብቂኝ ውስጥ ከተተው፡፡

 

 

የተሟላ ወንበርና ጠረጴዛ ፣ደረጃውን የጠበቀ መረጃ ሊሠበሰብ የሚችል መሣሪያ ማግኘቱ ለጋዜጠኞቹ አዳጋች ቢሆንም ተስፋን የሰነቁት ጋዜጠኞች ግን  ሲችሉ ኘሮግራም ሣይችሉ ደግሞ ዜና እየሰሩ ለኢትዮጵያ ራዲዮ ብሄራዊ አገልግሎትና ለኢትዮጵያ ቴሌቪዥን መላክን ተያያዙት

 

 

የክልሉ ጋዜጠኞቹ ደከመኝ ሠለቸኝ ሣይሉ አይገቡም እየገቡ የሠበሰቧቸውን  መረጃዎች ወደ ማዕከል ቢልኩም የተላከው ዜናም ሆነ ኘሮግራም በተፈለገው ጊዜ መተላለፍ አለመቻል ባስ ሲልም የውሃ ሽታ መሆን የጋዜጠኞቹን ልፋት መና ያስቀረ ነበር፡፡

 

ደክመውና ለፍተው ክልላችንን ያስተዋውቅልናል ሲሉ የላኩት መረጃም የውሃ ሽታ መሆን በተቋሙ ሠራተኞች ላይ እየዋለ እያደረ ቁጭትንወደ መፍጠር ተሸጋገረ፡፡  እና ጋዜጠኞቹ ከቢሮአቸው ጋር መከሩ ዘከሩ፤ በመጨረሻም  የወቅቱን ችግር የጋዜጣ ህትመት በመጀመር በትቂቱም ቢሆን መፍታት እንደሚቻል የጋራ ድምዳሜ ላይ ደረሱ፡፡ ታህሣስ 7 1987 ዓ/ም ግን  ቀዳሚነትን ያነገበው በኩር ጋዜጣ የበኩርና ህትመቱ አንድ ተባለ፡፡

 

በ8 ያህል ገፆቹ ጥቂት አምዶችን ያቀፈው በኩር ጋዜጣ በየሣምንቱ በ4000 ኮፒ መታተሙ በኢትዮጵያ ክልሎች የጋዜጣ ህትመት ጅማሮ የቀዳሚ ዙፍን ላይ እንዲደምቅ አደረገው፡፡

 

ሣምንታዊ የበኩር ጋዜጣም በአማራ ክልል የሚዲያ ጅማሮ ታሪክ ውስጥ ፈር ቀዳጅ ይሁን እንጂ ለጋዜጣ የሚሆነውን መረጃ ሰብስቦ ለህትመት የማብቃቱ ስራ ግን  ውስብስብ ከመሆኑ ባለፈ አሰልች ገፅታም ነበረው፡፡

 

አስፈላጊ መረጃዎችን፤ ፎቶዎችን፤ በምላጭ ቆርጦ ለጥፎ አዋዶ ለህትመት ማብቃቱ በወቅቱ ለነባሩ ጋዜጦች እልህ አስጨራሽ ተግባር ይሁን እንጂ የክልላቸው ህዝብ መረጃ የሚያገኝበት መንገድ አናሣ መሆን እንቅልፍ የነሣቸው የቢሮው ጋዜጠኞች በጋዜጣ ህትመቱ ሣይወሰኑ ሌላ ሃሣብ ዘየዱ፡፡ እናም የበኩር ጋዜጣ ህትመት መጀመሩ በ4ት ወራት ልዩነት ውስጥ በኩር መጽሔትን ለንባብ አበቁ፡፡

 

 

በ3ት ወር አንድ ጊዜ በ1000 ኮፒ ብዛት ለአንባቢያን መድረስ የጀመረው በኩር መጽሄት በሚዳስሣቸው ሃሣቦችና በሚያቀርባቸው ይዘቶች ጥንካሬ ምክንያት በርካታ አንባቢያን ማፋራት ቻለ፡፡

 

በተመሰረተ በአጭር ጊዜ ውስጥ የራሱን ሣምንታዊ ጋዜጣና  የ3ት ወር መጽሔት

ማሣተም የጀመረው ማስታወቂያ ቢሮ  የበኩር ህትመት ጅማሮው አንድ አመት ውስጥ  ሌላ የታሪክ ምዕራፍ ተሸጋገረ፡፡ ወቅቱ ደግሞ 1988 ዓ/ም ሲሆን ዋናኛ ክዋኔው ደግሞ የክልሉ መንግስት ያሉትን ቢሮዎች በአዲስ መንገድ ማደራጀቱ ነበር፡፡

 

በአዲሱ አደረጃጀት መሠረትም ለ3ት ዓመታት በቢሮ ደረጃ ሲንቀሣቀስ የነበረው ማስታወቂያ ከባህል ቱሪዝም ጋር ተቀላቅሎ ባቱማን ፈጠረ፡፡

 

 ከ1987 ዓ/ም የክልሉ ሚዲያዎች አዲስ አደረጃጀት ይደረግ እንጂ ከበኩር ጋዜጣዎች አማራጭ መረጃ ሊሰጥ የሚችል ሚዲያ በተፈለገው አለመሟላት እርስ ምታት ሆኖ እንደቀጠለ ነበር፡፡ይሁን እና  የክልሉ መንግስት ከሲዊድን አለም አቀፍ የልማት ድርጅት ጋር በመሆን በባህር ዳር ከተማ የራዲዮ ስቱዲዮ ለመገንባት ስምምነት መድረሣቸው ተሰማ፡፡ ይህም ተስፋን ከማጫር ባለፈ ጉጉትን ወለደ፡፡

 

እና የራዲዮ ስቱዲዮ ግንባታው በወርሃ ግንቦት 1989 ዓ/ም ሙሉ ለሙሉ መጠናቀቁን ተከትሎ የማይደርስ ይመስል የነበረው ጊዜ ደረሰ፡፡

 

 

ግንቦት 16 ቀን 1989 ዓ/ም በኢትጵያ ክልሎች የራዲዮ ኘሮግራሞች ጅማሮ የቀዳሚነት ምዕራፍን የገለጠው የራዲዮ ኘሮግራም በኢትዮጵዮ ራዲዮ ብሔራዊ አገልግሎት 594 ኪ.ኸርዝ መካከለኛ ሞገድ ላይ የጅማሬ ስርጭቱ ተሰማ፡፡  የአማራ ብሔራዊ ክልል ድምፅ፡፡    

 

 

ሲዳና የክልሉ መንግስት ከ4 ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ  ወጪ ያደረጉበት የአማራ ብሔራዊ ክልል ድምፅ ለጊዜው ዘመናዊነትን የተላበሰ ስቱዲዮ ባለቤት መሆኑን ተከትሎ የክልሉ ራዲዮ ዘርፍ ጅማሮ ወደ አዲስ ትንሣኤ ተሸጋገረ፡

 

 

በእየዕለቱ ከምሽቱ 1 ስዓት እስከ 2 ስዓት በኢትዮጵያ ራዲዮ 594 ኪ.ኸርዝ መካከለኛ ሞገድ ላይ ይሰራጭ የነበረው አማራ ብሔራዊ ክልል ድምፅ ዜና ጨምሮ ጥቂት ኘሮግራሞችን ለአድማጮቹ ማድረስ ቀጠለ፡፡

 

 

ስለክልሉ የሚወራበት ዕለታዊ የ1ስዓት የራዲዮ ስርጭት መጀመሩ ለዓመታት ሲማስኑ ለነበሩት ለተቋሙ ጋዜጠኞች እርካታን ቢሰጥም ስርጭቱ በራስ ራዲዮ አንቴና የሚስራጭ አለመሆኑን ተከትሎ ችግሮች መስተዋላቸው ቀጠለ፡፡

 

 

በበኩር ጋዜጣ ጋዜጣ ብኩርና በ1987 ዓ/ም የተሟሸው የአማራ ብሔራዊ ክልል ጅማሮ በ1989 ዓ/ም የአማራ ብሔራዊ ክልል ድምፅ የራዲዮ ኘሮግራም መጀመሩን ተከትሎ የመገናኛ ብዙሃን ስራው ፈር እየያዘ መጣ፡፡

በ2ቱ ሚዲየሞች መጀመር ምክንያት በጋዜጠኞች የታየው የስራ ትጋት ተቋሙ የቴሌቪዥን ኘሮግራም መጀመርን እንዲያልም መንገድ ጠርጎለታል፡፡ ይህንን ለማሣካት ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጋር ስምምነቶች ተደረጉ፡፡በመጨረሻም ወርሃ ሚያዝያ 1992 ዓ/ም የአማራ ብሔራዊ ክልል የቴሌቪዥን ኘሮግራም ለአየር በቃ፡፡

 

 

በኢትዮጵያ ክልሎች የቴሌቪዥን ኘሮግራም ስርጭት አጀማመር ታሪክ የቀዳሚነትን መንበር ያለው የአማራ ብሔራዊ ክልል የቴሌቪዥን ኘሮግራም ሲጀመር ሣምንታዊ የ3ዐ ደቂቃ የአየር ስዓት ነበረው፡፡ በዚህ የ3ዐ ደቂቃ ምጣኔ የክልሉን ገፅታ ማስተዋወቅ የቴሌቪዥን ኘሮግራሙ ተቀዳሚ ትኩረት ነበር፡፡

 

 

 በተመደበለት 30 ደቂቅ የአየር ጊዜ  ዜናን ሣይጨምር  የገፅታ ዘገባዎች ላይ ያተኮረም የአማራ ብሔራዊ ክልል የቴሌቪዥን ኘሮግራም በየሣምንቱ ለአየር ይበቃ ዘንድ በርካታ ሂደቶችን ጠይቋል፡፡

በተለይ ግን ዘርፍ ለክልሉ አዲስ መሆኑን ተከትሎ የችግሮች ስፋት ጥልቅ ነበሩ፡፡

 

 

በውጣ ውረዶቹ እየተፈተነ ለችግሮች እጅ ሣይሠጥ ከጋዜጣ አልፎ ክልላዊ የቴሌቪዥን ኘሮግራም የጀመረው ማስታወቂያ ቢሮ በ1993 ዓ/ም  ወደ ሌላ የታሪክ ምዕራፍ ተሸጋገረ፡፡ በአዋጅ ቁጥር 56/93 መሠረት በቢሮው ውስጥ የነበሩት  ሚዲየሞች በአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ስር እንዲጠቃለሉ ተደረገ፡፡ ድርጅቱም   የራሱ ስራ አስኪያጅ እንዲኖረው በቦርድ እንዲተዳደር ተጠሪነቱም ለክልሉ አስፈፃሚ እንዲሆን አዋጁ በግልፅ አስቀመጠ፡፡

 

 

ለዓመታት በተበጣጠሰ መንገድ ሲታትርና ሲጓዝ የቆየው የነበረው የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ራሱን ችሎ እንዲጓዝ መደረጉ በተቋሙ ዛሬነት ላይ ትልቅ መሠረት ነበርው፡፡  ለዚሁም ድርጅቱ ራሱን ማስተዳደር በጀመረ በ1 ዓመት ልዩነት ውስጥ የባህር ዳርና አካባቢዋ ህዝብ ታላሚ ያደረገ የኤፍ ኤም ራዲዮ ጣቢያ እንካችሁ አለ፡፡

 

ኤፍ ኤም ባህር ዳር 96.9

 

 

ሚያዚያ 22 1994 ዕለታዊ 2 ስዓት ስርጭት ይዞ ወደ አድማጮቹ መድረስ የጀመረው ኤፍ ኤም ባህር ዳር 96.9  የጅማሬ ጥንስሱ ዛሬ ላይ በየክልሉ ለተቋቋሙት የኤፍ ኤም ራዲዮ ጣቢያዎች  መሠረት ነበር

 

 

ለባህር ዳርና አካባቢ ብቻ ሣይሆን ለክልሉም አዲስ የነበረው ኤፍ ኤም ባህር ዳር ዕለታዊ የ2ት ስዓት ስርጭት ውስጥ  በጀመረ በቅናት ልዩነት ውስጥ ስርጭቱ ወደ 4 ስዓት አሣድጐም ነበር?በእርግጥ በስዓቱ መስፋት ጋር በርካታ ችግሮች ጅማሮውን ቢፋታተኑትም፡፡

 

በአዋጅ በተሰጠው ስልጣን ራሱን  ማስተዳደር ከጀመረ በ1 ዓመት ልዩነት ውስጥ የኤፍ ኤም ባህር ዳር ስርጭት እውን ያደረገው የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት መሠረታዊ የሚባል ማሻሻያ በበኩር ጋዜጣ ላይ አደረገ፡፡

 

 

 

አዲሱን ማሻሻያ ተከትሎ የበኩር ገፆቹ ከ8 ወደ 22?ከፍ አሉ  ጥቂት የነበሩት አምዶችም ከገጹ ማደግ ጋር ተሻሻሉ፡፡   በ4000 ቅጅ የተጀመረው የህትመት ስራም ወደ 10,000 ሺ ቅጅ ከፍ አለ፡፡

 

ይህ ብቻ አይደለም ለበኩር ጋዜጠኞች ፈተና የነበረው የህትመት ስራ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እልባት አገኘ፡፡

 

 

 

 

በ1985 ዓ/ም በአማራ ክልል መሠረቱ የተጣለው የብዙሃን መገናኛ ስራ 1ዐዓመታትን ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የጋዜጣ ህትመት የራዲዮና የቴሌቪዥን ኘሮግራሞች ስርጭት ጀምሯል፡፡  ይህም የሚዲያዎቹ ጅማሮ በሃገሪቱ ክልሎች የሚዲያ ታሪክ ጉዞ ላይ ፈር ቀዳጅነትን አላብሶታል፡፡

 

 

ተቋሙ ከተበጣጠሰ አሰራር ተላቆ ወደ እራሱን ወደ መቻል አደረጃጀትም ተሸጋግሯል፡፡ይህም ድርጅቱ ዛሬ ላይ ለደረሰበት የእድገት ጉዞ መሠረት የጣለ ሆነ፡፡ 9 ዓመታትን ለሁሉም ሚዲየሞቹ መጀመር የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት በ1994 ዓ/ም የጅማሮ ታሪኩን ከደመደመ በኋላ በ1995 ዓ/ም ጀምሮ በአየር ስዓት በሰው ሃይል እንዲሁም በቁሣቁስ ረገድ መሠረተ በሚባለ ሂደት የእድገት ጉዞውን አቀጣጥሎአል፡፡

 

 

“የእድገት ምዕራፍ” ከ1995-2005

ክፍል 2

No automatic alt text available.

የሀገራችን የሚዲያ ታሪክ  ሲወሣ ቀድሞ ወደ ስራ የገባው የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት እነሆ ዛሬ 20ኛ ዓመቱ የልደት በዓሉ ላይ ነግሷል፡፡

ድርጅቱ ዛሬ ላይ ለመድረስ በተለይ ከ1985 እስከ 1994 ዓ/ም ባሉት ዓመታት ውስጥ ያከናወናቸው የሚዲያ ዝርጋታ ተግባራት ዋነኛ መሠረቱም ናቸው?

እናም ከ1995 ዓ/ም ጀምሮ በተከታይ ባሉ 10 ዓመታት ውስጥ ደግሞ ድርጅቱ የተጓዘበት የእድገት ምዕራፍ ሌላው የተቋሙ አስገራሚ ገፅታው ነው?

ከጅማሮ በኋላ ያለፋት 10 ዓመታት የድርጅቱ የእድገት ዜና መዋዕል እነሆ ልንዘከር ነው፡፡

መሸጋገሪያ 1995 ዓ/ም ከዛሬ 10ት ዓመታት በፊት በአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት

ታሪክ ውስጥ በጉልህ የሚጠቀስ ታሪካዊ ወቅት ነገሩ እንዲህ ነው እዋጅ ቁጥር 56/93ን ተከትሎ የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት በራሱ እንዲተዳደር ተጠሪነቱም ለክልሉ አስፈፃሚ እንዲሆን ምክትል ስራ አስኪያጅም እንዲኖረው ተደረገ

የተጠሪነቱ ጉዳይ በግልፅ የተቀመጠለት የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት በ1995 ዓ/ም ከበኩር መጽሔት ህትመት ጋር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የተፍታበት ጊዜ ነበር፤ ለምን ቢሉ ደግሞ በወቅቱ የነበረው ማስታወቂያ ቢሮ የመጽሔት ህትመት በመጀመሩ ምክንያት የድግግሞሽ ስራ ለማስቀረት በሚል በአደረጃጀት ለውጥ የተሟላው የእድገት ጉዞ 1996 ዓ/ም መግባቱን ተከትሎ በሚዲም ወደ አየር ስዓት ጭማሬ ተሸጋገረ፤ በዋናነትም ከ5 ዓመት በፊት በሣምንታዊ የ30 ደቂቃ የተጠነሰሰው የአማራ ብሔራዊ ክልል የቴሌቪዥን ኘሮግራም ወደ ሣምንታዊ የ1 ስዓት የአየር ጊዜ ተሸጋገረ፤ ይህም ለሣምንት 1 ቀን ብቻ ይተላለፍ የነበረው የቴሌቪዥን ኘሮግራም ወደ ሁለት ቀን ከፍ አለ

1996 ላይ ቴሌቪዥን ስርጭቱ ላይ የአየር ስዓት ማሻሻያ ያደረገው የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅቱ በወራት ልዩነት ውስጥ በኤፍ ኤም ባህር ዳር 96.9 የቀን ስርጭት ላይም የስዓት ጭማሬ አከናውኖ ነበር፡፡ በማሻሻያው መሠረትም በቀን 4 ስዓት ብቻ ይተላለፋ የነበረው ኤፍ ኤም ባህር ዳር ወደ 6 ስዓት አደገ

በክልላዊ የቴሌቪዥን ስርጭቱና በኤፍ ኤም ሬዲዮም ላይ የስዓት ጭማሬ ያደረገው የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ከ1996 መጨረሻ ጅማሮ በአንድ ጉዳይ አትኮሮ ነበር ይህም በዋናነት የራሱን የማሠራጫ አንቴና በመትከል የተደራሽነቱ አደማሱን ማስፋት ላይ ምስጋና ለክልሉ መንግስትና ለሲዊድን አለም አቀፈ የልማት ድርጅት ይሁን አንድ የማሠራጫ አንቴናው ችግር ለመቅረፍ ከዘጌ ከተማ የተከላ ስራው ተጀመረ

ግንቦት 11 1997 ዓ/ም በአማራ ክልል የሬዲዮ ኘሮግራም ጉዞ ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ የማሠጠው ዜና ተበሠረ፣ 11 ሚሊዮን ብር ወጭ የተደገበትና 801 መካከለኛ ሞገድን የተሸከመው የማሠራጫ አንቴና የተከላ ስራው ተጠናቆ የመመረቁ ዜና ተበሠረ

ለ9ኝ ዓመታት ያህል ለተቋሙ ሠራተኞች ጭንቀት የነበረው ጊዜ የማሠራጭ ጣቢያ በጉልህ ተፋታ፣ በቀን ለ1 ስዓት ብቻ ይሠራጭ የነበረው የአማራ ክልል ራዲዮ ከ1 ስዓቱ ጋር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ተለያየ፡፡

በ9 ዓመታት ያህል በምሽት 1-2 በኢትዮጵያ ራዲዮ ብሔራዊ አገልግሎት 594 ኪ ኸርዝ  መካከለኛ ሞገድ ላይ ሲሠራጭ የነበረው የአማራ ብሔራዊ ክልል ድምፅ ከአመታት ወደ አድማጮቹ ደረሰ ይህም በተቋሙ የራዲዮ ዘርፍ ውስጥ ትልቅ አስተዋጽኦ ነበረው አዲሱ የማሠራጫ ጣቢያ ተከትሎ የቀን ስርጭቱ 1 ስዓት ብቻ የነበረው የአማራ ክልል ራዲዮ ወደ 6 ከፍ አለ አዳዲስ ኘሮግሞች በጣቢያው ላይ መንሸራሸር ጀመሩ

የ801 መካከለኛ ሞገድ የማሠራጫ ጣቢያ ዛሬ ላይ መተከሉን ተብሎ የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት በራዲዮ ተደራሽነቱ ላይ ስርነቀል የሆነ ለውጥን እንዲያይም እድል ሠጥቶታል፡፡

በ1997 ዓ/ም የራዲዮ ተደራሽነቱ በጉልህ የፈታው የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ከ2 ዓመታት በኋላ በ1995  ዓ/ም በቴሌቪዥን ስርጭቱ ላይ የስፖት ጭማሮ አድርጐ ነበር፣ በማሻሻያው መሠረት  ከ1996 ዓ/ም ጀምሮ ሣምንታዊ ስርጭቱ የ1 ስዓት የነበረው የአማራ ክልል ቴሌቪዥን ኘሮግራም ወደ 3 ከፍ አለ

በየጊዜው በሚዲሞች ላይ የአየር ስዓት ማሻሻያዎች እያደረገ የተደራሽነት ችግሩ እየፈታ የተሠጠውን ተልዕኮ በፅኑ መሠረት ላይ መከወኑን የቀጠለው የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ከ1999 ዓ/ም ጀምሮ በውስጣዊ አደረጃጀቱ ላይ ልዩ ልዩ ስራዎችን ሲያከናውን ቆይቶ ነበር፡፡ ይሒም ውስጣዊ አቅም በማሣደግ ሠፋፊ ስራዎችን እንዲያከናውን በር

ከፍቶለታል፤

በየአመቱ በለውጥ ምዕራፍ ውስጥ ማለፍን ግብ ያደረገው የአማራ ብዙሃን ድርጅት ከ2000 ዓ/ም መጨረሻ ጀምሮ በተለይ በክልላዊ የቴሌቪዥን ስርጭቱ ላይ አስደማሚ የስዓት ጭማሬን አድርጐል ይህም ማሻሻያ በሣምንት ለ3  ይተላለፍ የነበረው የአማራ ክልል የቴሌቪዥን ኘሮግራም ወደ 7 ስዓት ከፍ አለ ይህም ከሣምንት 3 ወደ ቀን የ1 ስዓት ስርጭት ተሸጋገረ፡፡

የአማራ ክልል የቴሌቪዥን ኘሮግራሞችን ከሣምንታዊ ስርጭት ወደ ቀን የ1 ስዓት እድሜ ያሸጋገረው የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት በክልላዊ የራዲዮ ስርጭቱ ላይም የስዓት ማሻሻያን በ2001 ዓ/ም እንደድ ነበር፡፡

በቀን ለ6 ስዓት ቆይታ የነበረወ ክልላዉ ራዲዮ ወደ 9 ስዓት ከፍ እንዲል ተደርጓል፡፡ ይህ ብቻ አይደለም ከ1997 ዓ/ም ጀምሮ በ801 ኪ.ኸርዝ መካከለኛ ሞገድ ይሠራጭ የነበረው ክልላዊ ራዲዮ በ6090 ኪ.ኸርዝ አጭር ሞገድም ስርጭት ጀምሮ ነበር፡፡

96.9 ዕለታዊ ስርጭቱ ከቀን 6 ስዓት ወደ 16 ለማሣደግ ችሏል፡፡ ይህም በዋናነት ድርጅቱ በዘጌ አራራት ተራራ ላይ የተከለም የኤፍ ኤም ራዲዮ አንቴና መጠናቀቁን ተከትሎ ነበር

ለዓመት በባህር ዳር ከተማ እንኳን በጥራት መሠማት ተሰኖት የነበረው ኤፍ ኤም  ባህር ዳር 96.9 አራራት በተተከለ አዲስ የማሠራጫ ጣቢያ አማካኝነት ስርጭቱ በክልሉ በርካታ ወረዳዎች መሰማት ችሏል፡፡

እነሆ ዛሬ 20ኛ ዓመት የልደት ሻማውን በመለኮስ ላይ የሚኘው የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት በአማራ ቋንቋ ከሚያስተላልፍቸው በርካታ ኘሮግራሞች በተጨማሪ በክልሉ ውስጥ የሚገኙ ብሔረሰቦች ራዲዮ ብሎም በጋዜጣ ቋንቋቸውን፣ባህላቸውንና ወጋቸውን እንዲያሣድጉ ብረቱ ጥረት እያደረገ ነው፡፡

ባለፋት 2ዐ አመታታ ከአማራ ክልል የእድገት ጉዞ ራሱን እያበለፀገ የመጣው የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት የተሰጠው ተልዕኮ እየተወጣ ዛሬ ላይ ደርሷል፡፡ ይሁንና ተቋሙ በዛሬነት ----ለመዝራት ግን ውጣ ውረዶችን አልፏል፡፡

ከዛሬ 2ዐ ዓመታት በፊት ባልተሟላ ወንበርና ጠረጴዛ ለውስጥ የሚያስፈልጉ የሚዲያ መሣሪያዎች እንኳን  ሣይኖራት ስራ የጀመረው የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት እነሆ ዞሬ ትናንትነቱ ታሪክ ወደ ሚያደርግ የታሪክ ምዕራፍ እየተሻገረ ነው፡፡

ድርጅቱ ዛሬ ከ20 ዓመታት በኋላ በሃገሪቱ የሚዲያ ታሪኩ ውስጥ ፋና ወጊናት የሚያስረደጉለት የሚዲያ ህንፃ ገንብቶ ለማስመረቅ በዝግጅት ላየ ይገኛለ፡፡

የአማራ ብሔራዉ ክልላዊ መንግስት ከ150 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ ያደረገበት ይህ እያሱ የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት የሚዲያ ህንፃ ከዘመኑ ጋር የዘመኑ የሚዲያ መሣሪያዎችተክለውበታል፡፡

በህንፃውስጥ ዓለም አቀፍ ደረጃዎች የጠበቁ 10 ያህል የራዲዮ  ስቱዲዮዎችና 2 የቴሌቪዥን ስቱዲዮዎች አቅመ ይዟል፡፡

Image may contain: screen and indoor

150 ሚልዩን ብር ውጭ ዛሬ የዘመናዉ የሚዲያ ህንፃ ባለቤት የሆነው የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት የተደራሽነት አድማሱን ለማስፊት በባህር ዳር  ካስገነባው የሚዲያ ህንፃ በተጨማሪ በደሴና በደ/ብርሃን ከተሞች 2ት የአዲሱ ኤፍ ኤም ራዲዮ  ጣቢያዎች ------የአገልግሎት አድማሱ እያስፋፋ ነው፡፡

ዛሬ አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የሚዲያ ህንፃ ባለቤት የሆነው የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ያለፋት ዓመታት የስራ ጊዜያት በአዲስ ምዕራፍ ለማድመቅ ከወዲሁ እየተዘጋጀ ነው፡፡

የትናንትና ተሞክሮውን  ለዛሬው በእርሾነት በመጠቀም የተሠጠውን ክልላዊ ኃላፊነት እየተወጣ የሚገኘው

የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ዛሬ ላይ ከተጎናጸፈው የለውጥ ምዕራፍ በተጨማሪ ለክልሉ ህዝብ ትኩስ መረጃ በወቅቱ ያገኝ ዘንድ በርካታ ትፅእኖችን መፍጠር እየቻለ ይገኛል ፡፡