በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ሦስት ትምህርት ቤቶችን ለማስገንባት ቃል ገቡ።

0
33

ባሕር ዳር፡ ታኅሳስ 20/2012ዓ.ም (አብመድ) በዋሽንግተን ዲሲ በተዘጋጀው የዳስ ትምህርት ቤቶችን ገጽታ መቀየሪያ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብር ከ 1ነጥብ 5 ሚሊዬን ብር በላይ ተሰብስቧል።

የዳስ ትምህርት ቤቶችን ገጽታ ለመቀየር በዋሽንግተን ዲሲ ዛሬ በተዘጋጀው የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብር የአማራ ተወላጅ ግለሰቦች ሦስት ትምህርት ቤቶችን ለማስገንባት ቃል ገብተዋል፤ በዝግጅቱም በጨረታ ብቻ 51 ሺህ 260 ዶላር ወይም 1ሚሊዮን 538 ሽህ የሚደርስ ብር ተሰብስቧል።

በዋሽንግተን ዲሲ የአማራ ማኅበር ከአልማ ጋር በመተባበር አንድ ትምህርት ቤት፣ ርብቃ ኃይሌ ከኒውዮርክ፣ አንድ ትምህርት ቤት፤ የማያ ሪልስቴት ባለቤት አቶ ዓለማየሁ መኮንት፣ አንድ ትምህርት ቤት ለማስገንባት ቃል ገብተዋል።

በሌላ በኩል የቲጂ ሲጋር ባለቤት እና ሥራ አስኪያጅ ትዕግስት ተገኘ፣ ለ100 ህጻናት ማሳደጊያና ማስተማሪያ፣ ለ100 አረጋዊያን መጦሪያ በጎንደር ከተማ ለማስገንባት ቃል ገብተዋል።

በሰሜን አሜሪካ ሰባት ግዛቶች ከሰሞኑ በተካሄዱ ሕዝባዊ ውይይቶች የአማራ ተወላጆች 7 የዳስ ትምህርት ቤቶችን ደረጃቸውን ጠብቀው ለማስገንባት ቃል መግባታቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

ዘጋቢ፡- አስማማው በቀለ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here