በኢትዮጵያ ዲያስፖራ ትረስት ፈንድ ከ5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ መሰብሰቡ ተገለጸ፡፡

0
24

ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 11/2012 ዓ.ም (አብመድ) በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከዲያስፖራ ትረስት ፈንድ የተሰበሰበውን ገንዘብ ይፋ አድርጓል፡፡

የኢትዮጵያውያን ዲያስፖራ ትረስት ፈንድ ከተመሠረተ አንድ ዓመት አስቆጥሯል፡፡ በነዚህ ጊዜያት ከአንድ ኢትዮጵያዊ ዲያስፖራ በቀን አንድ የአሜሪካ ዶላር በመሰብሰብ ላይ ነው፡፡

እስካሁን በተሠራው ሥራ ከ5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ተሰብስቧል፡፡ ገንዘቡ ከ25 ሺህ 645 ኢትዮጵያውያን ዲያፖራዎች የተሰበሰበ ነው ብሏል በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ፡፡

እንደ ኤምባሲው መረጃ በ46 ምዕራፎች በ77 ሀገራት ከሚኖሩ ዜጎች ገንዘቡን ማግኘት ተችሏል፡፡ የኢትዮጵያውያን ዲያስፖራ ትረስት ፈንድ ሙሉ በሙሉ በበጎ ፍቃደኞች የሚሰጥ ነው፡፡

ገንዘቡም ሙሉ በሙሉ ለተለያዩ ፕሮጀክቶች የሚውል እንደሆነ በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍጹም አረጋ በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡

ምንጭ፦ በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here