በኮሮና ቫይረስ የመያዝና የመሞት መጠን እየጨመረ መሆኑ ተገለጸ፡፡

0
40

በቻይና ሁቤይ ግዛት በአዲሱ የኮሮና ቫይረስ የሚያዙና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በክፍተኛ መጠን መጨመሩ ተገለጸ፡፡

በሁቤይ ግዛት በአዲሱ አደገኛ ቫይረስ 242 ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉና ይህም ከወረርሽኙ መቀስቀስ አንስቶ ከፍተኛው አሀዝ መሆኑ ታውቋል፤ በቻይና በኮሮና ቫይረስ የሞቱትን ሰዎች ቁጥር ከ1 ሺህ 350 እንዲበልጥም አድርጎታል፡፡ 14 ሺህ 840 ሰዎች ደግሞ በበሽታው መያዛቸው ተረጋግጧል፤ በአጠቃላይ በቻይና በቫይረሱ የተጠቁት ሰዎች ቁጥርም ወደ 60 ሺህ ተጠግቷል፡፡

በሁቤይ የኮሙዩኒስት ፓርቲው ኃላፊ ተነስተውም በሻንጋይ ፓርቲ ኃላፊ ተተክተዋል፤ የውኃን ከተማ የፓርቲ ኃላፊም ከኃላፊነታችው ተነስተዋል፡፡ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በተነሳባት ሁቤይ ግዛት እንዲህ ዓይነት ፖለቲካዊ እርምጃ ሲወሰድ ከወረርሽኙ በኋላ የመጀመሪያው ነው ተብሏል፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ

በአብርሃም በዕውቀት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here