ባሕር ዳር ከነማ ከሰበታ ከነማ ጋር በባሕር ዳር ዓለም ዓቀፍ ስታድየም የሚያደርገው ጨዋታ ተጠባቂ ነው፡፡

0
55

ባሕር ዳር: የካቲት 01/2012 ዓ.ም (አብመድ) በኢትዮጵያ የወንዶች እግር ኳስ ፕሪሚየር ሊግ 13 ሳምንት ጨዋታ ባሕር ዳር ከነማ እና ሰበታ ከነማ ዛሬ ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ላይ በባሕር ዳር ዓለም ዓቀፍ ስታድየም ይጫወታሉ፡፡

ባሕር ዳር ከነማ ባለፈው ሳምንት ከወልቂጤ ከነማ ጋር በነበረው ጨዋታ 7 ተጫዋጮች በጉዳት አለመሰለፋቸውን ያስታወሱት አሰልጣኙ ፋሲል ተካልኝ በዛሬው ጨዋታም የተወሰኑ ተጫዋቾች ወደ ጨዋታ እንደማይመለሱ ተናግረዋል፡፡

የዛሬው የባሕር ዳር ከነማ ተጋጣሚ ሰበታ ከተማ እኩል 17 ነጥብ በመሰብሰብ በግብ ክፍያ ከባሕር ዳር ከነማ ተሽሎ 5ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፤ ባሕር ዳር ከነማ 17 ነጥብ ቢሰበስብም በሰበታና ወልቂጤ ከተማ በግብ ክፍያ ተበልጦ 7ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡

ተመሳሳይ ውጤት ሰብስበው መገናኘታቸው የዛሬውን ጨዋታ ተጠባቂ አድርጎታል፤ውጤቱ ከአቻ ውጭ ከተጠናቀቀ የደረጃ ለውጥ የሚያስከትልም ይሆናል፡፡

ባሕር ዳር ከነማ በሜዳው ያለመሸነፍ ልምዱን ተጠቅሞ ሊያሸንፍ እንደሚችል ብዙዎች ግምት እየሰጡ ይገኛሉ፡፡

ዘጋቢ፡- ዳግማዊ ተሠራ
ምስል፡- ከባሕር ዳር ከነማ ደጋፊዎች ማኅበራዊ ገጽ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here