አምራች ኢንዱስትሪዎች የውጭ ምንዛሬ በሚጠይቁበት ጊዜ ከምርት በኋላ የሚያሥገኙትን የውጭ ምንዛሬ ሠርተው ሊያቀርቡ እንደሚገባ ተመላከተ፡፡

0
6
ባሕር ዳር፡ መስከረም 06/2013ዓ.ም (አብመድ) የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ከጨርቃጨርቅ፣ አልባሳት እና ቆዳ አምራች ኢንዱስትሪ ማኅበራት ጋር የዘርፉን ችግሮች ለመፍታት የሚያስችል ጥናት ቀርቦ ወይይት ተደርጎበታል፤ በውይይቱ ላይ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል እንደገለፁት ማንናቸውም አምራች ኢንዱስትሪ ከውጭ ለሚያሥገባው ጥሬ ዕቃ መግዣ ለሚጠይቀው የውጭ ምንዛሬ ዕቃውን ካስገባና እሴት ጨምሮ በማምረት ወደ ውጭ ገበያ ልከው የሚያሥገኙትን የውጭ ምንዛሬና ተኪ ምርት ላይ በማዋል የሚያድነውን የውጭ ምንዛሬ በዝርዝር ጥናት ላይ ተመሥርተው መረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
 
‘‘የዘርፉን ዕድገት ማሻሻል የሚቻለው አቅም አለን እያሉ በመፎከር አይደለም’’ ያሉት ሚኒስትሩ የዘርፉ ተዋናዮች የማኅበራቸውን አቅም በማሳደግ ለዘርፉ ዓለም አቀፍ የገበያ ትስስር፤ የሰው ኃይል ስልጠና፣ የፋብሪካ ምርትና አገልግሎት ችግር ፈች ጥናት ሊያከናውኑ የሚችሉ ዓለማቀፋዊ ዕውቀት ያላቸውንና ዕውቀታቸውን ለሌሎች በማካፈል ትውልድን ለማሳደግ የሚሠሩ ሠራተኞችን ቀጥሮ በማሠራትና የዘፉርን ችግር ለመፍታት ለመንግሥት የፖሊሲ አማራጭ ማሳየትና የመፍትሔው አካል መሆን እንዲሆኑም አስገንዝበዋል፡፡
 
በመድረኩ የጨርቃጨርቅና አልባሳት እንዲሁም የቆዳ ዘርፍ ማኅበራት የዘርፉን ችግር ሊፈታ የሚያስችል የመፍትሔ አቅጣጫ ጠቋሚ ጥናት ቀርቦ ውይይት መደረጉን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here