አርሰናል ኡናይ ኢሚሬይን አሰናበተ፡፡

0
39

የሰሜን ለነደኑ አርሰናል በውጤት መዋዠቅ ውስጥ የሚገኙትን አሰልጣኝ ኡናይ ኢሚሬይን አሰናብቷል፡፡

ለ22 ዓመታት በአርሰን ዌንገር ተይዞ የነበረውን ዙፋን ተቆጣጠረው የነበሩት ስፔናዊ አሰልጣኝ ከዙፋናቸው ወርደዋል፡፡ ኡናይ ኢሚሬይ ከ18 ወራት ቆይታ በኋላ ነው ከአርሰናል አሰልጣኝነት የተባረሩት፡፡ ሦስት ጊዜ በተከታታይ ከሀገራቸው ቡድን ሲቪያ ጋር የዩሮፓ ሊግ ዋንጫን በማሸነፍ የዩሮፓ ሊግ ‹ስፔሻሊስት› የሚባሉት ኢሚሬይ በፈረንሳዩ ኃያል ቡድን ፓሪስ ሴንት ዠርሚንም አስደናቂ የሚባል ጊዜን አሳልፈው ነበር፡፡

ኢሚሬይ አርሰን ዌንገር ግንቦት 2018 ከአርሰናል መልቀቃቸውን ተከትሎ ነበር ኢሚሬትስን የረገጡት፡፡ ወደ አርሰናል አሰልጣኝነት ሲመጡም በዌንገር የመጨረሻዎቹ ዘመናት ዋንጫ ርቆት የነበረውን አርሰናልን ወደቀደመ ኃያልነቱ ይመልሱታል ተብሎ እምነት ተጥሎባቸው ነበር፡፡ ነገር ግን ያለስኬት 18 ወራትን ተጉዘው ከኃላፊነታቸው ተነስተዋል፡፡

በአርሰናል አሰልጣኝነት ቆይታቸውም በዩሮፓ ሊግ ለፍጻሜ ከመድረሳቸው በስተቀር ያሳኩት አንድም ዋንጫ የለም፡፡ አሰልጣኙ በፕርሚየር ሊጉ እያደረጉት ያለው ጉዞ ደካማ ሲሆን ትናንትና በሜዳቸውና በደጋፊያቸው ፊት በጀርመኑ ኢንትራክት ፍራንክፈርት መሸነፋቸው ለመባረራቸው ዋና ምክንያት ሆኗል፡፡ አርሰናልን የቀድሞው የቡድኑ አማካኝና ረዳት አሰልጣኝ ፍሬዲሊ ሉንበርግ በጊዜያዊነት እንሚያሰለጥኑት ታውቋል፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ
በታርቆ ክንዴ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here