‹‹እስካሁን በሜዳችን ያደረግናቸውን ስድስቱንም ጨዋታዎች አሸንፈናል፤ ነገም ለማሸነፍ ወደ ሜዳ እንገባለን፡፡›› አስለጣኝ ስዩም ከበደ

0
222

14ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ ጨዋታዎች ከዛሬ ጀምሮ ሲደረጉ የአምነው አሸናፊ መቀሌ 70 እንድርታ ከሐዋሳ ከተማ ጋር ይጫወታል፡፡ በ13ኛ ሳምንት በሜዳውና በደጋፊው ፊት በፋሲል ከነማ የተሸነፈው መቀሌ 70 እንደርታ በተከታታይ ሁለት ጨዋታዎችን በሜዳው ሲያደርግ ዛሬ የካቲት 7 ቀን 2012ዓ.ም ከሐይቆቹ ጋር ይጫወታል፡፡ ያለፉትን ሁለት ዓመታት ከተለያዩ ቡድኖች ጋር በመሆን በተከታታይ ሁለት የፕሪሚዬር ሊግ ዋንጫዎችን ያነሱት አሰልጣኝ ገብረመድኅን ኃይሌ ከዋንጫ ፍክክሩ ላለመውጣት በዛሬው ጨዋታ የተለዬ የአጨዋወት ስልት ይዘው እንደሚመጡ ይጠበቃል፡፡ ኳስን አደራጅቶ በመጫዎት የሚታወቁት ሐይቆቹም ጥሩ የጨዋታ ፍሰት እንደሚያሳዩ ይጠበቃል፡፡ ጨዋታው ቀን 9፡00 ይደረጋል፡፡

ፕሪሚዬር ሊጉ ነገ ሲቀጥል የሳምንቱ ታላቅ ጨዋታ ጎንደር ላይ ይደረጋል፡፡ አጼዎቹን ከፈረሰኞቹ የሚያገናኘው ጨዋታ በጉጉት ይጠበቃል፡፡ በደረጃ ሰንጠረዡ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙት ሁለቱ ቡድኖች የነገውን ጨዋታ በድል ለመወጣት የሚያደርጉት ጨዋታ የቡዙዎችን ትኩረት ስቧል፡፡ ፋሲል ከነማ በዚህ የውድደር ዓመት በሜዳው ያደረጋቸውን ጨዋታዎች ሁሉንም በድል መወጣቱ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ደግሞ ከጥቂት ጨዋታዎች ወዲህ እያሳዬ ያለው አቋም አስፈሪ መሆን ጨዋታውን ተጠባቂ አድርጎታል፡፡

ፋሲል ከነማ ከቅዱስ ገዮርጊስ ጋር የሚያደርጉትን ጨዋታ አስመልክቶ አስተያየት የሰጡት የፋሲል ከነማ አሰልጣኝ ስዩም ከበዳ ‹‹እስካሁን በሜድችን ያደረግናቸውን ስድስቱንም ጨዋታዎች አሸንፈናል፤ ነገም ለማሸነፍ ወደ ሜዳ እንገባለን›› ብለዋል፡፡ ነገ የሚደረገውን ጨዋታ ማሻነፍ ደግሞ በፕሪሚዬር ሊጉ አናት ላይ ለመውጣት ስለሚያግዝ ‹‹ተጨዋቾች፣ ደጋፊው እና ሁሉም የስፖርት ቤተሰቦች በጥንካሬ እየሠሩ ነው›› ብለዋል፡፡ ‹‹በስብስባችን ምንም የተጎዳ ተጨዋጭ የለንም›› ያሉት አሰልጣኙ ከመቀሌ ጨዋታ በኋላ የተነቃቃውን ስሜት ይዘን ለማሸነፍ ወደ ሜዳ እንገባለን ብለዋል፡፡

በሌላ ጨዋታ ባሕር ዳር ከነማ ወደ ወላይታ ተጉዞ ከጦና ንቦች ጋር በዲቻ ሲታዲዬም ይጫወታል፡፡ ስለጨዋታው ያላቸውን ቅድመ ዝግጅት ለአብመድ አስተያዬታቸውን የሰጡት አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ወሳኝ ተጫዋቾቻቸውን በጉዳት እንዳጡ ተናግረዋል፡፡ ፍፁም ዓለሙ፣ ወሰኑ አሊ፣ ሳለምላክ ተገኝ እና ፍቅረማሪያም ጉዳት ላይ እንደሆኑ ነው የተናገሩት፡፡ ‹‹ምንም እንኳን ወሳኝ ተጫዋቾቻችን ከቡድናችን ጋር ባይኖሩም የተቻለንን አድርገን ለማሸነፍ እንጨዋታለን፤ የተጎዱ ተጫዋቾች ደግሞ በሚቀጥለው ሳምንት ይመለሳሉ›› ብለዋል አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ፡፡

በሌላ ጨዋታ ጅማ አባጅፋር ከድሬዳዋ ከተማ፣ ስሁል ሽሬ ከሀዲያ ሆሳዕና እና አዳማ ከተማ ከወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡ የ14ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ሰኞም ሲቀጥሉ በደቡብ ደርቢ አዲስ አዳጊው ወልቂጤ ከተማ ከሲዳማ ቡና ጋር ሲገናኝ ሰበታ ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ይጫወታሉ፡፡ ፕሪሚዬር ሊጉን ቅዱስ ጊዮርጊስ በ26 ነጥብና በ11 ንጹሕ ግብ ሲመራው ፋሲል ከነማ በ25 ነጥብና በ13 ንጹሕ ግብ 2ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

የአምናው አሸናፊ መቀሌ 70 አንደርታ በ22 ነጥብና በ2 ንጹህ ግብ ሦስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ ሀድያ ሆሳዕና፣ ድሬደዋ ከተማና ኢትዮጵያ ቡና ወራጅ ቀጣናው ላይ ይገኛሉ፡፡ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን ሙጅብ ቃሲም ከፋሲል ከነማ በ13 ጨዋታዎች 13 ግቦችን በማስቆጠር በሰፊ ልዩነት ይመራዋል፡፡

ዘጋቢ፡አዳሙ ሽባባው

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here