የሴካፋ ዋንጫ የሚጀመርበት ጊዜ ተገለጸ፤ አህመድ ሙሳ 100 ተማሪዎችን ዩኒቨርሲቲ ሊያስተምር ነው፡፡

0
16

ባሕር ዳር፡ ሕዳር 13/2012 ዓ.ም (አብመድ) የምሥራቅና መካከለኛው አፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ ከሁለት ሳምንት በኋላ በዩጋንዳ መካሄድ ይጀምራል፡፡

የምሥራቅና መካከለኛው አፍሪካ (ሴካፋ) የወንዶች ብሔራዊ ቡድኖችና ከ17 ዓመት በታች የሴቶች ውድድሮች በዩጋንዳ አስናጋጅነት ከሁለት ሳምንታት በኋላ መካሄድ ይጀምራሉ፡፡

በታንዛንያ የሴካፋ የሴቶች ዋንጫ ጨዋታ ላይ በተሰጠ መግለጫ እንደተመላከተው በገንዘብ ድጋፍ (ስፖንሰር) ማጣት በየጊዜው ሲራዘም የቆዬው የወንዶች ሲካፋ ዋንጫ ውድድር ከሕዳር 27 እስከ ታኅሳስ 9 ቀን 2012ዓ.ም ይካሄዳል፡፡

ሩዋንዳ ራሷን ከውድድሩ ከማግለሏ በቀር ሁሉም የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት እንደሚሳተፉ ይጠበቃል፤ ሊቢያ ደግሞ ከሰሜናዊ የአፍሪካ ሀገራት በተጋባዥነት ትሳተፋለች፡፡

ቡሩንዲ በውድድሩ የሚሳተፈውን ቡድኗን ዝርዝር አሳውቃለች፤ ኢትዮጵያን ጨምሮ ሌሎች ሀገራት ደግሞ በቅርቡ የቡድን አባላቶቻቸውን እንደሚያሳውቁ ይጠበቃል ያለው ሶከር ኢትዮጵያ ነው፡፡

የናይጀሪያው ብሔራዊ ቡድን አምበል አህመድ ሙሳ የናይጀሪያ 100 ተማሪዎችን ወጭ ሸፍኖ ዩኒቨርሲቲ ሊያስተምር ነው፡፡ ሙሳ ለመገናኛ ብዙኃን እንዳስታወቀው በናይጀሪያ ካኖ ግዛት በሚገኘው ‹ስካይላይን ዩኒቨርሲቲ› የ100 ተማሪዎችን ወጭ ሸፍኖ ሊያስተምር ነው፡፡

የ27 ዓመቱ የንስሮቹ አምበል የተማሪዎችን መደበኛ የትምህርት ወጭ ከመሸፈን በተጨማሪ ለተጓዳኝ የትምህርት ማበልጸጊያዎች ማለትም ለስፖርትና አቻ ለአቻ ስልጠናዎች የሚሆኑ ወጭዎችንም ይሸፍናል፡፡ ‹‹እኔ በትምህርት ፋይዳ የማምን ሰው ነኝ፤ ሕልማችሁን እንድትሆኑ ድጋፍ በማድረጌ ደግሞ ደስታዬ ወደር የለውም›› ብሏል ለዕድሉ ተጠቃሚዎች ሲናገር፡፡ (ኦል አፍሪካ)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here