የባዲገዝ በዓል በኮምቦልቻ ከተማ እየተከበረ ነው::

0
25

ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 16/2012 ዓ.ም (አብመድ) ዓመታዊው የኮምቦልቻ አካባቢ የእሸት በዓል ‹ባዲገዝ› እየተከበረ ነው፡፡ ባዲገዝ ‹‹ባዕድም ይግዛ፤ ያደረም ይግዛ›› የሚል ትርጓሜ ያለው ቃል እንደሆነ የአካባው ሰዎች ያስረዳሉ፡፡ የቃሉ ትርጉም ሁሉም ሰው መተባበር ወይም መተጋገዝ እንዳለበት የሚያሳይ እንደሆነም ነው የተገለጸው፡፡

የእሸት በዓል (ባዲገዝ) ከ1979 ዓ.ም ጀምሮ አተጠናከረ መልኩ መከበር እንደጀመረ የአካባቢው የሀገር ሽማግሌዎች ይናገራሉ፡፡ በበዓሉ የአካባቢ ነዋሪዎች መሬት ያበቀላቻቸውን የእህል ዘሮች ሁሉ እሸት ይዘው በአንድ ቦታ በመቅረብ በጋራ የበላሉ፤ የእንስሳት ተዋጽኦ የሆኑ ምግቦችም የበዓሉ አካል ናቸው፡፡

በዕለቱ የተለያዩ የእንስሳት እና እህል ዘሮች ይቀርባሉ፤ የቀረበውን እሸት ደግሞ ነዋሪዎች በሀብት መጠን፣ በሃይማኖት፣ በዘር፣ በጾታና በዕድሜ ሳይከፋፋሉ በጋራ ይመገባሉ፡፡

ይህ በዓል በየዓመቱ በጥቅምት ወር ይከበራል፡፡ የበዓሉ አከባበር አስተባባሪ ሃጂ አሊ ሽፋው እንደነተናገሩት የአካባቢ ነዋሪዎች በዓሉን በሠላም ካጠናቀቁ በኋላ ዓመቱ የሠላም እንዲሆን ዱዓ (ጸሎት) ያደርጋሉ፤ ለሚቀጥለው የባዲጋዝ በዓል ይዘው የሚመጡትን እሽትም ቃል ይገባሉ (ስለት ይሳላሉ)፡፡

ዘጋቢ፡- ጀማል ይማም -ከኮምቦልቻ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here