የብሔራዊ የእንስሳት ጥበቃ ኢንስቲትዩት የተለያዩ ክትባቶችን ለሀገር ውስጥና ለውጭ ሀገራት እያቀረበ ነው፤ አበረታች አፈጻጸም ማሳየቱም ተመላክቷል፡፡

0
21

ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 28/2012 ዓ.ም (አብመድ) የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የግብርና፣ አርብቶ አደርና አካባቢ ጥበቃ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የብሔራዊ የእንስሳት ጥበቃ ኢንስቲትዩት የ2012 በጀት ዓመት የአንደኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ላይ ተወያይቷል፡፡
በውይይቱ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ማርታ ያሚ (ዶክተር) የሰው ኃይል የማሟላትና የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች መከናዎናቸውን ገልጸው የክትባት ምርትን በሚመለከት በዚህ ሩብ ዓመት 90 ሚሊዮን ዶዝ የተለያዩ የባክቴሪያ እና ቫይረስ ክትባቶች ለማምረት ታቅዶ 74 ነጥብ 3 ሚሊዮን ዶዝ ክትባቶችን ማምረት መቻሉን ገልጸዋል፡፡ በአጠቃላይ የሩብ ዓመቱ ክንውን ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ከፍ ያለ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የክትባት ሽያጭን በሚመለከት በሩብ ዓመቱ ለሀገር ውስጥ ደንበኞች 68 ነጥብ 7 ሚሊዮን ዶዝ ክትባቶችን በማቅረብ 37 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር ለማግኘት እንዲሁም ለውጭ አገር ደንበኞች 8 ሚሊዮን ዶዝ ክትባቶች በማቅረብ 6 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ እንደነበርነም አብራርተዋል፡፡ በውጤቱም በሀገር ውስጥ 103 ሚሊዮን ዶዝ በማቅረብ 53 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር መገኘቱንና ለውጭ አገር ደግሞ 610 ሺህ ሚሊዮን ዶዝ ተሸጦ 760 ሚሊዮን ብር መገኘቱን አብራርተው የሽያጭ ክንውናቸውም ካለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከፍ ያለ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

በሌላ በኩል የኤሌትሪክ ኃይል ዝርጋታ አለመከናወን፣ የውጭ ምንዛሪ እጥረት በመኖሩ የግብአት ዕጥረት ማጋጠሙ፣ የመብራት መቆራረጥና የመሣሪያዎች ተደጋጋሚ ብልሽት እና በፌዴራል የእንስሳት ሀብት ዘርፍ ለክልሎች ክትባት የተገዛበት ከብር 34 ሚሊዮን 531 ሺህ በላይ ያልተከፈላቸው መሆኑ በችግነት ዋና ዳይሬክተሯ ሪፖርቱን ባቀረቡበት ወቅት ገልጸዋል፡፡
ከዶሮ ክትባት ጥራት፣ የለውጥ ሥራዎችን ከተቋሙ ባሕሪ ጋር ማዛመድና ተጀምረው በሂደት ላይ ያሉ ሥራዎችን ዳር ማድረስ እንደሚገባም አስተያዬት መሰጠቱን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በማኅበራዊ ገጹ አስታውቋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here