የኮሮና ቫይረስ በሽታን ይፋ ያደረጉት ሐኪም ሞት ቁጣ ቀስቅሷል፡፡

0
510

በቻይና ውሃን ግዛት የተቀሰቀሰውን የኮሮና ቫይረስ በሽታ ይፋ ያደረጉት ዶክተር ሊ ዌነሊንግ ሞት በቻይና ቁጣ መቀስቀሱን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ ሐኪሙ የሞቱት በቫይረሱ የተጠቁ ሕሙማንን ሲያክሙ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ተከትሎ ነው፡፡

በአውሮፓውያኑ ባለፈው ታኅሣስ ላይ ‹‹ሳርስ መሠል አደገኛና ገዳይ ቫይረስ ተቀስቅሷል›› የሚል ማስጠንቀቂያ ለሕክምና ጓደኞቻቸው መልእክት መላካቸውን ተከትሎ ፖሊስ ‹‹ሐሰተኛ አስተያዬት ነው የሰጠኸው›› በሚል በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ ጀምሮባቸው እንደነበር ዘገባው አመላክቷል፡፡

የሐኪሙ ሞት በቻይና ማኅበራዊ ሚዲያ በኩል መሠራጨቱን ተከትሎ ቁጣ መቀስቀሱ ነው የተሠማው፡፡ በሽታው እንደተቀሰቀሰ በመንግሥት በኩል ለመደበቅ መሞከሩና ሐኪሙ ማጋለጣቸው ቅሬታ ፈጥሮ ነበር፡፡

አንዳንዶች የዶክተር ሊን ሞት ከቻይና የመናገር ነፃነት ጋር ማያያዛቸው ነው የተነገረው፡፡ የቻይና የፀረ-ሙስና ተቋም ከዶክተር ሊ ሕልፈት ጋር በተያያዘ ምርመራ እንደሚጀምርም አስታውቋል፡፡

የቻይና መንግሥት ቀደም ሲል ለኮሮና ቫይረስ የሰጠው ምላሽ አነስተኛ መሆኑን ማመኑ የሚታወስ ነው፡፡ በበሽታው እስካሁን 636 ሰዎች ሕይታቸውን አጥተዋል፤ 31 ሺህ 161 ደግሞ በቻይና ብቻ በበሽታው ተይዘዋል፡፡

በአብርሃም በዕውቀት

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here