የዚምባብዌ ምክትል ፕሬዝዳንት ባለቤት ከሙስና ጋር በተገናኘ በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

0
21

ባሕር ዳር፡ ታኅሳስ 06/2012ዓ.ም (አብመድ) የምክትል ፕሬዝዳንቱ ኮኒስታንቲኖ ቺዌንጋ ባለቤት ሜሪ ሙባይዋ በሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር፣ በማጭበርበርና የገንዘብ ምንዛሬ ቁጥጥር ሥርዓት በመጣስ ነው የተከሰሱት፡፡ የ38 ዓመቷ ሜሪ ዕለተ ቅዳሜ የተያዙ ሲሆን ዛሬ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የዚምባብዌ ፀረ-ሙስና ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

የኮሚሽኑ ቃል አቀባይ ጆን ማካሙር ተጨማሪ መረጃዎችን ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡ ሜሪ ሙባይዋም ስለተጠረጠሩበት ጉዳይ ለመገናኛ ብዙኃን አስተያየት አልሰጡም፡፡ በአውሮፓውያኑ 2019 ቺዌንጋ በፕሬዝዳንት ምናንጋግዋ በምክትል የሀገር መሪነት ተሹመዋል፡፡

የዚምባብዌ ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ሙስናን ለማስቆም ጫና ውስጥ ገብቷል፤ እንደ ዓለም አቀፉ የግልጸኝነት ተከታታይ ድርጅት (ኢንተርናሽናል ትራንስፓረንሲ ዋችዶግ) ሙስና ሀገሪቱን በዓመት 1 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ያሳጣታል፡፡

ከአውሮፓውያኑ ጥቅምት – ግንቦት 2019 ሙባዋ ቁሳቁሶችን ከውጭ በማስገባት ስም 919 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ወደ ደቡብ አፍሪካ በማዛወር ተወንጅለዋል፤ ሙባይዋ ግን ይህን ተግባር አለመፈጸማቸውን ሲገልጹ ቆይተዋል፡፡

ምንጭ፡- አልጀዚራ
በኪሩቤል ተሾመ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here