ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ ከተባበሩት ዐረብ ኤሜሬቶች ምክትል ፕሬዚዳንት፣ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር እና የዱባይ ገዢ የተከበሩ ሼክ መሀመድ ቢን ረሺድ አልመክቱም ጋር ተወያዩ።

0
49

ሼክ መሀመድ ጠቅላይ ሚንስትሩን በተቀበሉበት ወቅት ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ኢትዮጵያን ለመለወጥ የሚያደርጉትን ጥረት እንዲሁም በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ ሠላም ለማስፈን የሚያከናውኑትን ሥራ እንደሚያደንቁ እና እንደሚደግፉ ገልፀውላቸዋል።

ውይይቱ በዱባይ እና በመላው ዐረብ ኤመሬቶች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ያነሷቸው ልዩ ልዩ ችግሮች በሚፈቱባቸውና ጥያቄዎች በሚመለሱባቸው መንገዶች ላይ አተኩሯል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይም ትናንት 300 ከሚሆኑ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ተወካዮች እና መሪዎች ጋር ባደረጉት ውይይት የቀረቡላቸውን ጥያቄዎች ለሼህ መሀመድ ቢን ረሺድ አንስተውላቸዋል፡፡

በኢትዮጵያውያን የሥራ ፈቃድ፣ የአምልኮ እና የትምህርት ቤት ግንባታ ቦታዎችን የማግኘት ጥያቄዎችና ተያያዥ ጉዳዮችን ዙሪያ ከልዩ ልዩ ኃላፊዎች ጋር እንደሚመክሩበትም ቃል ገብተዋል፡፡ በአቡዳቢ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ማሠሪያ የሚሆን ቦታም ፈቅደዋል።

ምንጭ፡- የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here