ፋሲል ከነማ ከሜዳው ውጭ ነጥብ ተጋርቷል።

0
37

የኢትዮጵያ የወንዶች ፕሪሚዬር ሊግ 1ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ ተካሂደዋል፤ ከሜዳው ውጭ ከአዳማ ከነማ ጋር የተጫወተው ፋሲል ከነማ ያለ ግብ አቻ ወጥቷል።

ሐዋሳ ከተማ በሜዳው ድሬ ዳዋ ከተማን 2ለ1 አሸንፏል። የዓመቱን የሊጉን የመጀመሪያ ግብ ያስቆጠረው ኤልያስ ማሞ በ15ኛ ደቂቃ አስቆጥሯል።

ሰበታ ከነማ በሜዳው በወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ 3ለ1 ተሸንፏል። ካርሎስ ዳምጠው በፍጹም ቅጣምት ምት አስቆጥሯል። የወልዋሎን ግቦች ካርሎስ ዳምጠው አንዷንና ሰመረ ሀፍታይ በ56ኛውና 90ኛው ደቂቃዎች ሁለቱን አስቆጥረዋል።

የአምናው ሻምፕዮን መቀሌ 70 እንደርታ ዘንድሮም ሊጉን በድል ጀምሯል፤ ሀድያ ሆሳዕናን በትግራይ ዓለማቀፍ ስታዲዬም አስተናግዶ 2ለ1 አሸንፏል።

ወላይታ ዲቻም ሲዳማ ቡናን 2ለ0 አሸንፏል። ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ወልቂጤ ከተማ አቅንቶ ያለግብ ነጥብ ተጋርቶ ተመልሷል።

ባሕር ዳር ከነማ ነገ ከጅማ አባ ጅፋር አዳማ ላይ ይጫወታል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here