ፋሲል ከነማ ከሜዳው ውጭ አሸነፎ የሊጉ መሪ መሆን ቻለ፡፡

0
79

በኢትዮጵያ የወንዶች እግር ኳስ ፕሪሚዬር ሊግ ዛሬ ወደ መቀሌ አቅንቶ ከመቀሌ 70 እንደርታ ጋር የተጫወተው ፋሲል ከነማ 2ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

ድሉ ፋሲል ከነማን የሊጉ መሪ መሆን ከማስቻሉም ባለፈ ከሜዳው ውጭ የነበረውን ተከታታይ ያለማሸነፍ ሥነ ልቦና የሚቀርፍ ጅምር ሆኗል፡፡

በ13ኛ ሳምንት ጨዋታው ፋሲል ከነማ ከሜዳው ውጭ ሲያሸንፍ ሁለቱን ግቦች ከመረብ ላይ ያሳረፈው የሊጉን ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት በሰፊ ልዩነት እየመራ የሚገኘው ሙጂብ ቃሲም እንደሆነ ቡድኑ በማኅበራዊ ገጹ አስታውቋል፡፡ ሙጂብ 13ኛ ሳምንት ላይ በደረሰው የፕሪሚዬር ሊጉ ውድድር 13 ግቦችን አስቆጥሯል፤ ተከታዩ የሲዳማ ቡናው አዲስ ግደይ 8 ግቦችን ነው ያስቆጠረው፡፡

ፋሲል ከነማ ማሸነፉን ተከትሎ ፕሪሚዬር ሊጉን በ25 ነጥብ ይመራል፤ የ13ኛ ሳምንት ጨዋታውን ገና ያላካሄደው ቅዱስ ጊዮርጊስ በ23 ነጥብ ይከተላል፡፡ ጊዮርጊስ አቻ ከወጣ ወይም ከተሸነፈ ዓፄዎቹ በመሪነታቸው ይቀጥላሉ፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here